1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኮሚሽን ለየመን ርዳታ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 30 2007

የአዉሮጳ ኮሚሽን በጦርነት እየወደመች ላለችዉ የመን የ 12 ሚሊዮን ይሮ ተጨማሪ ርዳታ የሰጠ መሆኑን ትናንት አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/1GBDE
Europäische Union Flaggen Brüssel
ምስል DW/A. Rönsberg

ከአራት ወራት በፊት በየመን በተከፈተዉ የአየር ድብደባና የርስ በርስ ጦርነት ሳብያ መላ የሀገሪቱ ህዝብ ለሞትና ሥደት የተጋለጠ ሲሆን የሀገሪቱ መሠረታዊ መዋቅሮችም በመፈራረስ ላይ መሆናቸዉ ታዉቋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች መርጃ ድርጅት ባወጣዉ መግለጫ በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የምግብ፤ የዉኃ፤ የመጠለያ የነዳጅና የመድሃኒት የመሳሰሉት መሠረታዊ ቁሳቁሶች እጥረት ያጋጠመ በመሆኑ አስከፊ እልቂት እንዳይከሰት ሲል ሥጋቱን ገልፆአል።


ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ