1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረት የሁለት ቀን ጉባኤ

ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2007

የአዉሮጳ ኅብረት የሀገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሁለት ቀን ጉባኤ የኅብረቱ ዋና መቀመጫ በሆነችዉ ብራስልስ ጀምረዋል። ሚኒስትሮቹ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስጋትነቱ እየተጠናከረ በመጣዉ በሽብር እንቅስቃሴና በሕገወጥ ወደአዉሮጳ ስለሚገቡ ስደተኞች ጉዳይ እንደሚነጋገገሩ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/1EpP3
Italien Rettungsschiffe Flüchtlinge
ምስል picture alliance/AP Photo

የኅብረቱ ፕሬዝደንትነትን መንበር የያዘችዉ ላቲቪያ 28 አባላት ያሉት ኅብረት የድንበር አካባቢዎችን አጠናክሮ ለመጠበቅ እንዲያስችለዉ በቂ ገንዘብ እንዲመደብ እየጠየቀች ነዉ። ባለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ብቻም ከሁለት መቶ ሺህ የሚበልጡ ጥገኝነት ጠያቂዎች በሕገወጥ መንገድ ወደተለያዩ የኅብረቱ ሃገራት መግባታቸዉ ተገልጿል። ስለሚኒስትሮቹ ጉባኤና መነጋገሪያ ነጥቦች ብራስልስ የሚገኘዉን ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ