1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረትና ሩሲያ ጉባኤ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 12 2005

የሩሲያዉ መሪ ቪላድሚር ፑቲን ዳግም የፕሬዝደትነት የስልጣን መንበር ከያዙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደብራስልስ በመጓዝ ከአዉሮፓ ኅብረት መሪዎች ጋ ተወያይተዋል።

https://p.dw.com/p/177lv
ምስል Reuters

ሁለቱ ወገኖች በአዉሮጳ ኅብረት ሀገሮች እና በሩሲያ መካከል መሠረታዊ በሆነዉ በኃይል አቅርቦት፤ ሞስኮ የሶርያን ቀዉስ አስመልክቶ በያዘችዉ አቋም፤ እንዲሁም በሩሲያ የሰብዓዊ መብት እና የተቃዉሞ ፖለቲካዉ ወገን አያያዝ ላይ ሰፊ ዉይይት አካሂደዋል። ሩሲያ ዜጎቿ ወደሌሎች የአዉሮጳ ሀገሮች ያለ ይለፍ እንዲሸጋገሩ ያቀረበችዉ ጥያቄም ዳግም ያነጋገረ ሲሆን ከ27ቱ የኅብረቱ መንግስታት ጋ ያላት የንግድና መሰል ግንንኙነቶችም ተነስተዋል። ዉይይቱ ሲያበቃ ዛሬ ከቀትር በኋላ የነበረዉን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለዉን የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ  አነጋግሬዋለሁ።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ