1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ምክር ቤት ምርጫ ፈረንሳይና ጉባኤ

ረቡዕ፣ ግንቦት 20 2006

በፈረንሳዩ ምርጫ ቀኝ አክራሪዎቹ ከፍትኛ ድምፅ ለማግኘታቸዉ ብዙዎች በሥልጣን ላይ ያለዉን የፕሬዳንት ፍራንሷ ኦሎንድን ሶሻሊስታዊ ፓርቲ ተጠያቂ ያደርጋሉ

https://p.dw.com/p/1C8Y3
ምስል Reuters

ፈረንሳይ ዉስጥ ባለፈዉ ዕሁድ ለአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት አባላት በተደረገዉ ምርጫ ቀኝ ፅንፈኛዉ ብሔራዊ ግንባር አብላጫ ድምፅ ማግኘቱ፤ የሐገሪቱን ፖለቲካዊ ጉዞ ግራ አጋቢ አድርጎታል።በመላዉ የሕብረቱ አባል ሐገራት በተደረገዉ ምርጫ ብሪታንያንና ጀርምንን በመሳሰሉ የሕብረቱ ትላልቅ አባል ሐገራት ቀኝ አክራሪዎች ያልተጠበቀ ዉጤት ቢያመጡም የፈረንሳይን ያክል ግን ትላልቅ ፓርቲዎችን ያስደነገጠ ዉጤት አላመጡም።በፈረንሳዩ ምርጫ ቀኝ አክራሪዎቹ ከፍትኛ ድምፅ ለማግኘታቸዉ ብዙዎች በሥልጣን ላይ ያለዉን የፕሬዳንት ፍራንሷ ኦሎንድን ሶሻሊስታዊ ፓርቲ ተጠያቂ ያደርጋሉ።የፓሪሷ ወኪላችን ሐይማኖት ጥሩነሕ አንዳድ የፓሪስ ነዋሪዎችን አነጋግራ የሚከተለዉን ዘገባ ልካልናለች-------ትናንት ብራስልስ-ቤልጂግ ተሰብስበዉ የነበሩት የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት መሪዎችም ክፉኛ ካስደነገጣቸዉ ከሰሞኑን ምርጫ የቀደመ የመነጋገሪያ ርዕሥ አልነበራቸዉም።መሪዎቹ የሕብረቱ መርሕ ከአዲሱ ምርጫ ዉጤት ጋር የተጣጠመ የሚሆንበትን ሥልት የሕብረቱ ምክር ቤት እንዲያርቀቅ ሐላፊነት ሠጥተዉታል።የሕብረቱን ኮሚሽን የወደፊት ፕሬዝዳንት ለመምረጥ የሚወዛገቡ ወገኖችንም የምክር ቤቱ ፕሬዝዳናት እንዲያደራድሩ መሪዎቹ ተስማምተዋል።መሪዎቹ ከሕብረቱ ሥራና አሠራር በተጨማሪ የዩክሬንን ምርጫ ዉጤትና ቀዉስም አንስተዉ ተነጋግረዋል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ አጭር ዘገባ ሎኮልናል።

ሐይማኖት ጥሩነሕ

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ