የአዉሮጳ ሕብረት ወታደራዊ ዘመቻ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 11 2007ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረት ሥደተኞችን በሜድትራኒያን ባሕር በኩል ወደ አዉሮጳ ለማስገባት የሚሞክሩ ሥደተኛ አዘዋዋሪዎችን የሚመታ የባሕር ጦር ሊያዘምት ነዉ።የሕብረቱ አባል ሐገራት የዉጪና የመከላከያ ሚንስትሮች ትናንት ባሳለፉት ዉሳኔ መሠረት ጠቅላይ ዕዙን ሮም-ኢጣሊያ ያደረገ ባሕር ሐይል በቅርቡ ይመሠረታል።ሚንስትሮቹ በነደፉት ዕቅድ መሠረት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤትን ይሁንታ እንዳገኘ ጦሩ እርምጃ ይወስዳል።የመብት ተሟጋችና የስደተኞች ተቆርቋሪዎች ግን የሕብረቱን የሐይል እርምጃ ዕቅድ አጥብቀዉ ተቃዉመዋል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ