1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

 የአዉሮጳ ሕብረት በጀት ለአፍሪቃ ቀንድ ስደተኞች

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 6 2010

የአዉሮጳ ሕብረት ከአፍሪቃ ወደ አዉሮጳ የሚገቡ ስደተኞችን በያሉበት ለመገደብ ለአፍሪቃ መንግስታት የገንዘብ ድጋፍን ጨምሮ የተለያዩ ርዳታዎችን እያደረገ ነዉ።የሕብረቱን እርምጃ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እየተቹት ነዉ

https://p.dw.com/p/2pRGD
Libyen Europa Migration Zustände in Flüchtlingslagern
ምስል Getty Images/AFP/T. Jawashi

(Beri.Brussel) EU Budget-Flüchtlinge am Horn von Afrika - MP3-Stereo

የአዉሮጳ ሕብረት  ለአፍሪቃ ቀንድ ሐገራት ስደተኞች እና ላስተናጋጆቻቸዉ ይረዳሉ ለተባሉ ፕሮጄክቶች ማስፈፀሚያ ከ176  ሚሊዮን ዩሮ በላይ መመደቡን አስታወቀ።ሕብረቱ የመደበዉ ገንዘብ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ6 የአፍሪቃ ሐገራት ሊሰሩ ለታቀዱ 13 ፕሮጄክቶች የሚዉል ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረት ከአፍሪቃ ወደ አዉሮጳ የሚገቡ ስደተኞችን በያሉበት ለመገደብ ለአፍሪቃ መንግስታት የገንዘብ ድጋፍን ጨምሮ የተለያዩ ርዳታዎችን እያደረገ ነዉ።የሕብረቱን እርምጃ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እየተቹት ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ