የአዉሮጳ ሕብረትና ቡሩንዲ
ማክሰኞ፣ የካቲት 8 2008ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረት የቡሩንዲን ሠላም ያዉካሉ ባላቸዉ የሐገሪቱ ፖለቲከኞች ላይ የምጣኔ ሐብት ማዕቀብ እንደሚጥል አስጠነቀቀ።ትናንት ብራስልስ-ቤልጂግ ተሰብስበዉ የነበሩት የሕብረቱ አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች እንዳስጠነቀቁት ቡሩንዲ ዉስጥ ሠላም ለማስፈን የሚደረገዉን ጥረት የሚያዉኩ ሐይላትን ሕብረታቸዉ በማዕቀብ ይቀጣል።ሚንስትሮቹ እንደሚሉት የቡሩንዲ ተቀናቃኝ ወገኖችን ለመሸምገል የሚደረገዉን ጥረት በተለይ የፕሬዝደንት ፔሪ ንኩሩንዚዛ መንግሥት እያደናቀፈ ነዉ።ማዕቀቡ መቼ እና በማን ላይ እንደሚጣል ግን ሚንስትሮቹ በግልፅ ያስታወቁት ነገር የለም። የብራስልሱ ወኪላችን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ