የአዉሮጳ ሕብረትና ስደተኞች
ረቡዕ፣ መስከረም 12 2008ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረት አባል መንግሥታት የሐገር አስተዳደር ሚንስትሮች ደቡባዊ አዉሮጳ የገቡ ስደተኞችን በኮታ ለመከፋፈል በአብላጫ ድምፅ ወሰኑ።ትናንት ብራስልስ-ቤልጅግ የተሠበሰቡት ሚንስትሮች በወሰኑት መሠረት የሕብረቱ አባል መንግሥታት ግሪክ፤ ኢጣሊያና ሐንጋሪ የሚገኙ አንድ መቶ ሥልሳ ሺሕ ስደተኞችን ይከፋፈላሉ።የሚንስትሮቹን ዉሳኔ ዛሬ የተሰየመዉ የመሪዎች ጉባኤ ያፀድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጭምሮ የስደተኞች መብት ተቆርቋሪዎችን የአዉሮጳ ሕብረትን ዉሳኔ ለስደተኞቹ ችግር መፍትሔ የማይሆን በማለት እየተቹት ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ