የአዉሮጳ ህብረትና ሩሲያ ጉባኤ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 28 2004ማስታወቂያ
ሶርያን ከእርስበርስ ጦርነት ለመታደግ የአረቡ ሊግና የተመድ የሰየሟቸዉ ልዩ የሰላም ልዑክ ኮፊ አናን ያቀረቡት የሰላም እቅድ ተግባራዊ መሆን አማራጭ የለዉም የሚል እንደሆነ የኅብረቱ ፕሬዝደንት ኸርማን ቫንሮምፖይ ገልጸዋል። ይህም ተግባራዊ እንዲሆን ሁለቱም ወገኖች በጋራ የየበኩላቸዉን ጥረት ማድረግ እንደሚኖርባቸዉም ሮምፖይ አመልክተዋል። ከሁለቱ ወገኖች የሁለት ቀናት ስብሰባና ዉይይት በኋላ ለጋዜጠኞች የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንና ሮምፖይ ለ50 ደቂቃዎች ያህል ጋዜጣዊ መግለጫ ቢሰጡም፤ ፑቲን ሶርያን የሚመለከት አንዳችም ሃሳብ አለመተንፈሳቸዉ ነዉ የተነገረዉ።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ