የአኺም ሽታይነር እና የሄለን ቢሲምባ አስተያየት
ሰኞ፣ መጋቢት 23 2005ማስታወቂያ
እኛ የተመድ ሰራተኞች ናይሮቢ፡ ሁሉም ስው ፣ ቲምቡክቱ ይሁን በርሊን፡ ዋሽንግተን ወይም ብራዚል የሚኖሩት ሁሉ የምናቀርባቸውን መረጃዎች መልዕክት እኩል በሚረዱልን ሁኔታ ላይ ጥገኞች ነን። ዶይቸ ቬለም ሰዎች ይቀራረቡ ዘንድ ከሚረዱት መገናኛ መድረክ መካከል አንዱ ነው። ስለዚህ ዶይቸ ቬለን ለወደፊቱ ስራው መልካም ዕድል እንመኝለታለን።
------------------------
በዳሬሰላም የሰብዓዊ እና የሕጋዊ መብቶች ተሟጋች ማዕከል ኃላፊ- ሄለን ኪጆ ቢሲምባ
ዶይቸቬለ ፡ በተለይ የኪስዋሂሊ ቋንቋ፡ ድምፃችን እንዲሰማ ሁሌም ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሮልን ቆይተዋል፤ ምክንያቱም፡ በታንዛንያ ብዙ ሕዝብ በኪስዋሂሊኛ ቋንቋ የሚሠራጨውን ዝግጅት ያዳምጣል። ይህ በጣም በጣም ጠቃሚ ነው። ሰዎች ብዙ መረጃዎችን ከዶይቸ ቬለ የኪስዋሂሊ ቋንቋ ክፍል ዝግጅት እንደሚያገኙ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ሰምቻለሁ።