1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአክባር ሐሼሚ ራፍሳንጃኒ የሕይወት ታሪክ 

ሰኞ፣ ጥር 1 2009

የኢራን አብዮት አባት ተብለው የሚቆላመጡት እና ከጎርጎሮሳዊው 1989-1997 ዓ.ም. በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉት አክባር ሐሼሚ ራፍሳንጃኒ በትናንትናው ዕለት በ82 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

https://p.dw.com/p/2VXGf
Akbar Haschemi Rafsandschani
ምስል picture alliance/dpa/Photoshot/A. Halabisaz

Beri. Berlin Nachruf Akbar Hashemi Rafsandschani - MP3-Stereo

ከአገሪቱ መንፈሳዊ መሪ አያቶላኽ አሊኻሚኒ ጋር ጥብቅ ግንኙነት የነበራቸው ራፍሳንጃኒ ኢራን በተፈተነችባቸው አደገኛ ጊዜያት ሁሉ የግንባር ሰው እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከኢራን ቀደምት ባለጠጎች መካከል አንዱ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ሥርዓት ውስጥ የለውጥ ደጋፊ የወግ አጥባቂዎቹ ተቺ የነበሩት አክባር ሐሼሚ ራፍሳንጃኒ ህልፈት ምዕራባውያኑን አሳዝኗል። ራፍሳንጃኒ ግለሰባዊ መብቶች እንዲከበሩ፤ ኢራንም ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ከገባችበት ውጥረት ተላቃ ግንኙነቷን እንድታሻሽል ወትዋች ነበሩ። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለሚካኤል የሕይወት ታሪካቸውን የሚዳስስ ዘገባ አጠናቅሮዋል።


ይልማ ሐይለሚካኤል


እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ