የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ፣ ያሠራጨው ደብዳቤ፣
ዓርብ፣ መስከረም 19 2004ማስታወቂያ
ለሀገሪቱ ጠ/ሚንስትርና ፕሬዚዳንት እንዲሁም ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ድርጅቶች ግልጽ ደብዳቤ መጻፉን ከአዲስ አበባ ታደሰ እንግዳው የላከልን ዘገባ ያስረዳል። አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ፣የመሠረታዊና የሰብአዊ መብቶች አለመከበር፤ የፖለቲካ ምኅዳሩ መጥበብ፤ የዴሞክራሲ መታፈንና ሌሎች የፖለቲካ ሂደቶችንና ዑደቶችን የዘረዘረበትን ደብዳቤ፤ የጠ/ሚንስትሩ ጽ/ቤትና የፕሬዚዳንቱ ቤተ-መንግሥትእንዳልተቀበሉት ተነግሯል።
ደብዳቤው ዛሬ፤ እንደገና፣ በይፋ፣ በፖስታ ቤት በኩል መላኩን የመድረኩ የሥራ አስፈጻሚና ፤ የአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትኅ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ አብራርተዋል።
ታደሰ እንግዳው
ነጋሽ መሐመድ