የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ወቀሳ18 ጥር 2007ሰኞ፣ ጥር 18 2007አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ትናንት በአዲስ አበባ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቶ የነበረ ሲሆን፣ የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች ሰልፍ ለመዉጣት በዝግጅት ላይ እንደነበሩ በፌዴራል ፖሊስ የኃይል ተግባርhttps://p.dw.com/p/1EQfwምስል picture alliance/dpaማስታወቂያ እንደተፈፀመባቸው የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ተክሌ በቀለ ለዶይቸ ቬለ ገለጹ። አንድነት በአባላቱ ላይ ተፈፀመ ስላለው ድብደባ ደረሰ ስላለው ጉዳት ከመንግሥት ጽሕፈት ቤት እና ከአዲስ አበባ መስተዳድር አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ስብሰባ ላይ ናቸው በመባሉ ሳይካሳ ቀርቶዋል። አርያም ተክሌ ነጋሽ መሀመድ