1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሮን ማረፊያ ሰፈር በአጋዴዝ ከተማ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 2009

ዩኤስ አሜሪካ በኒጀር የአብራሪ የለሽ(የድሮን) ጦር አይሮፕላን ማረፊያ ሰፈር በመገንባት ላይ ትገኛለች። ከአጋዴዝ ከተማ በስተደቡብ አሜሪካ ለጀመረችው ፀረ ሽብር ትግሏ ማራመጃ እየገነባችው ያለው ይኸው የድሮን ማረፊያ ሰፈር 500 በ500 ሜትር ስፋት እንዳለው ይገመታል። የአጋዴዝ ከተማ ነዋሪዎች በዚሁ ያሜሪካውያን ፕሮጀከት አልተደሰቱም።

https://p.dw.com/p/2U8KU
USA stationieren Drohnen in Niger
ምስል picture-alliance/dpa

niger - MP3-Stereo


በኒጀር ከአጋዴዝ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የታስካንታላም መንደር የምትኖረው ፋጢማ በአሁኑ ጊዜ ወደ ገበያ ለመሄድ ከበፊቱ ሶስት እጥፍ መንገድ መጓዝ አለባት። ፋጢማ 180,000 ነዋሪ ወዳላት አጋዴዝ ወተት ለመሸጥ በየቀኑ  ትጓዛለች። ዩኤስ አሜሪካ በአጋዴዝ አቅራቢያ አብራሪ አልባ የጦር አይሮፕላን(ድሮን) ማረፊያ ሰፈር መገንባት ከያዘች ወዲህ  ፋጢማ አንድ ሰዓት ተኩል እንደሚወስድባት በቅሬታ ገልጻለች።
«  ፈለግንም አልፈለግንም፣  አጋዴዝ ማደር ተገደናል። ልጆች ታድያ ብቻቸውን መቆየት አለባቸው። በአሜሪካውያኑ የጦር ሰፈር የተነሳም ለነገታው ነው ወደ ቤታችን መመለስ የምንችለው። ቤተሰባችንን እንደሚገባው ለማስተዳደር እና ኑሯችንን  ለመምራት እንችል ዘንድ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ እንፈልጋለን። ምክንያቱም፣ ለኅልውናችን በአጋዴዝ ገበያ ላይ ጥገኛ ነን። »
ሌላው ያካባቢው ነውሪ ኢብራሂም ማንዞም በሁኔታው አልተደሰተም።
« የአጋዴዝ ነዋሪ  ነን፣ እና በየቀኑ ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ላይ ትልቆቹ አይሮፕላኖች ሲያርፉ እና እንደገና ሲመለሱ መጡ አያለሁ፣ ምን እንደሚያጓጉዙ ማንም አያውቅም። » 
የግንባታውን ሂደት በተመለከተ የአካባቢው ነዋሪዎች ግልጽ መረጃ የላቸውም። ዩኤስ አሜሪካ በአፍሪቃ ስለምታደርገው የጦር ትብብር ምርምር የሚያካሂዱት  በሎስ አንጀለስ የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር አዳም ሙርም በኒጀር ስለተጀመረው ግንባታ ብዙም ማለት እንደማይችሉ ነው ያስታወቁት።  
በሳተላይት ፎቶዎቹ መሰረት፣ የአንድ ሰፈር ግንባታ  ይታያል። ከአጋዴዝ ከተማ በስተደቡብ አንድ 500 በ500 ሜትር የሚገመት የአይሮፕላን መነሻ እና ማረፊያ ቦታ እየተሰራ ነው።  ይህ በጣም ትልቅ ነው። »
በሌሎቹ  ባለፉት ጊዚያት በተካሄዱት አጫጭር  የዩኤስ አሜሪካ  ጦር ፕሮጀክቶች አንፃር፣ በተለይ ፣ ለግንባታው የተመደበውን የገንዘብ መጠን ሲመለከቱት፣ የአጋዴዙ ለረጅም ጊዜ የታሰበ ሳይሆን እንዳልቀረ ሙር ገልጸዋል።
«ዘ ኢንተርሴፕት» በተባለው የኦንላይን መጽሄት ዘገባ መሰረት፣አሜሪካውያን 100 ሚልዮን ዶላር ለዚሁ ሰፈር ግንባት ከፍለዋል።ይህ መጠን የአሜሪካውያን መከላከያ ሚንስቴር፣ «ፔንታገን» ከሰጠው መረጃ በእጥፍ በልጦ ነው የተገኘው። የፔንታገን ቃል አቀባይ ሚሼል ባልዳንዛ ለፈረንሳይ ዜና ወኪል በሰጡት መግለጫ ወጪው 50 ሚልዮን እንደሆነ ነበር ያስታወቁት። ከዚህ በተጨማሪም ይኸው ሰፈር ያሜሪካ ጦር ሰፈር ይሆን የኒጀር መሆኑንም ተናግረዋል።ኒጀር ዩኤስ አሜሪካ እና አጋሮችዋ በዓለም አቀፉ ሽብርተኝነት አንጻር በጀመሩት ትግል ላይ ዋና ስልታዊ ተጓዳኝ ናት። በተለይ ማሊ፣ናይጀሪያ እና ሊቢያ በማግሬብ ለሚንቀሳቀሰው ከአል ቃይዳ ጋር ቅርበት ያለው ቡድን፣ አክሚ፤፣ ለቦኮ ሀራም እና ለእስላማዊ መንግሥት መሸሸጊያ እና መንቀሳቀሻ ናቸው። አዳም ሙር የአጋዴዝ ሰፈር  ለድሮን የስለላ በረራ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ይገምታሉ።
«በመጀመሪያ ደረጃ በሰሜናዊ ኒጀር እና በደቡባዊ ሊቢያ የመረጃ ስለላ ስራ  ላይ የሚያገለግል ይመስለኛል። ለዚሁ ስራ ከመዲናይቱ ኒያሜ አጋዴዝ ትመረጣለች፣ምክንያቱም ቅርብ ነው። »
እስከአሁን አሜሪካውያኑ ከኒያሜ ነው የተባሉትን አካባቢዎች የሚሰልሉት። «ዋኅንግተን ፖስት ዘገባ መሰረት፣ ተመሳሳይ አብራሪ የለሽ የአይሮፕላን ሰፈር ቱኒዝያም ውስጥ ለመገንባት እቅድ አለ። በስተሰሜን ከቱኒዝያ፣ በስተደቡብ ደግሞ ከአጋዴዝ እስካዛሬ ድረስ ከፊክል ሰሃራ ተጓድሎ የነበረውን የመረጃ ስብሰባ ስራ በጠቅላላ ለመሰብሰብ እንደሚያስችል ሙር ይገምታሉ።
«በ2014 ዓም ነበር ገና የኒጀር ፕሬዚደንት ማሃማዱ ኢሱፉ በአጋዴዝመረጃ ለመሰብሰቢያ እና ለቁጥጥር ስራ  የአብራሪ አልባ ጦር አይሮፕላን ሰፈር እንዲገነባ ስምምነታቸውን የሰጡት።  ከዚሁ አካባቢ ህገ ወጥ የሚባለው ብዙ እያከራከረ ያለው የድሮን ጥቃት ሊካሄድ ይችል ይሆን በሚል ለተነሳው ጥያቄ ሙር የማይሆንበት ምክንያት የለም ሲሉ ይመልሳሉ።
«ሊሆን ይችላል። ይሁንና፣ አስተናጋጇ ሀገር ኒጀር ይህን ትፈቅዳለች ወይ ነው ጥያቄው። ይህ በጣም ሰበበኛ እና አሳሳቢ ጉዳይ ነው። »
በኒያሜ ካለው እና በአጋዴዝ እየተገነባ ከሚገኘው ሰፈር በተጨማሪ ብዙም ያልተነገረለት ሌላ ሶስተኛ ሰፈር መኖሩን ሙር ገልጸዋል። ይከውም በከአጋዴዝ በስተሰሜን 250 ኪሜ ርቆ በሚገኘው አርሊት በተባለው ቦታ ቢያንስ ከአንድ ዓመት ወዲህ ዩኤስ አሜሪካ አንድ ልዩ ኃይላት ሰፈር አላት። በልዩ ኃይላት ሰፈር ወይም በንዑስ ኩባንያ ሽፋን ስም በብዙ ቦታዎች በርካት እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ተናግረዋል። ዩኤስ አሜሪካ ካለፉት 10 ዓመታት ወዲህ በአፍሪቃ ግልጽ የጦር ሰፈር ኅልውና ከማድረግ ተቆጥባለች። ይሁንና፣  « መጀመሪያ ኒያሜ ላይ የድሮን ሰፈር፣ አሁን ደግሞ በአጋዴዝ ተመሳሳይ ግንባታ ጀምረዋል።  በአጋዴዝ እየሰሩት ያለውን ሰፈር በቀላሉ ልትደብቀው አትችልም። ይህ ከኒጀር መንግስት ጋር የቆየ ወዳጅነት ግንኙነት እንዳላቸው ነው የሚያሳኢ,ው። ኒጀርም ለሰሜን እና ምዕራብ አፍሪቃ ለሚደረገው ጸረ ሽብር ትግል መነሻ ሆና ማገልገል ላይ መሆንዋል አረጋግጧል። »
አጋዴዝ  ለፀረ ሽብሩ ትግል መናኸሪያ እየሆነች ያለበት ድርጊት ችግር ውስጥ ሊጥላቸው እንደሚችል የከተማይቱ ነዋሪዎችን እንዳላስደሰተ አንዱ ነዋሪ ላዋል ኡዱሉ በስጋት ገልጸዋል።
« በርግጥ ይህ ለኒጀር ሕዝብ ጥሩ አይደለም።  ሁኔታዎችን አስተማማኝ አያደርግልንም። በአንፃሩ እማንፈልገው ጦርነት ውስጥ እንድንገባ ነው የሚያደርገን።»
ኒጀር ከጅቡቲ ቀጥላ በአፍሪቃ ሁለተኛዋ ዋና የዩኤስ  አጋር  መሆኗን ሙር ገምተዋል።    እንደሚታወቀው፣ በአፍሪቃ ትልቁ እና «ለሞንየ» የተባለው የአሜሪካውያን ጦር ሰፈር ጦር ሰፈር ጅቡቲ ይገኛል። እንግዲህ ይኸው ያሁኑ አስተዳደር በአፍሪቃ የተከተለው ፖሊሲ በስዩሙ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ዘመነ ስልጣን እንዴት እንደሚቀጥል፣ በትራምፕ አማካሪዎች ላይ ጥገኛ እንደሚሆን  ሙር ገልጸል።

Karte Niger Agadez Englisch
Boko Haram
ምስል Java
USA stationieren Drohnen in Niger
ምስል picture-alliance/dpa

አርያም ተክሌ/ፍሪደሪከ ሚውለር ዩንግ

ሂሩት መለሰ