የአባይ ግድብ ውዝግብና ስምምነት
እሑድ፣ መጋቢት 27 2007ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን መሪዎች ስለ ታላቁ የአባይ ግድብ በቅርቡ የተፈራረሙት ስምምነት እስካሁን በመካከላቸው ሰፍኖ የቆየውን ጥርጣሬ የማስወገድና ከአባይ ውኃ አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ሌሎች ችግሮችን ደረጃ በደረጃ የማቃለል ተስፋ ተጥሎበታል ። የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ መርሆዎች መግለጫ Declaration of Principles on Ethiopian Renaissance Dam የተባለው ይኽው ስምምነት በበጎ እርምጃነቱ ቢወደስም ልዩ ልዩ ጥያቄዎችንም ማስነሳቱ አልቀረም ። አንዳንድ የመስኩ ባለሞያዎች በስምምነቱ ኢትዮጵያ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ በሌሎችም መስኮች ከግድቡ ተጠቃሚ ልትሆን የምትችልበትን እድል አልተጠቀመችም ሲሉ ይተቻሉ ። መንግሥት በበኩሉ ስምምነቱ ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ወደ ኋላ የሚል አይደለም በማለት ይከራከራል ። በመጪው እሁድ የሚተላለፈው እንወያይ የአባይ ግድብ ውዝግብና ስምምነት በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ነው ።
ኂሩት መለሰ
ልደት አበበ