1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቡነ ጴጥሮስ ሐዉልት መመለስና የሕዝብ አስተያየት

ሰኞ፣ ጥር 30 2008

ከ79 ዓመት በፊት በፋሺስት ጣሊያን ወታደሮች እጅ የተሰዉት የአቡነ ጴጥሮስ ሐዉልት ትናንት እሁድ ጥር 29 ቀን ቀድሞ ወደ ነበረበት ስፍራ በክብር መመለሱ በርካቶችን አስደስቶአል።

https://p.dw.com/p/1Hrg0
Äthiopien Statue von Abune Petros
ምስል DW/Y. G. Egziabher


ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም በፋሺስት ጣሊያን ወራሪዎች በጥይት ተደብድበዉ የተገደሉት የአቡነ ጴጥሮስ ሐዉልት፤ በመሬት ዉስጥ የሚያልፈዉን የአዲስ አበባን ቀላል የባቡር መጓጓዣ መስመር ግንባታ ሲባል ሚያዝያ 24 ቀን 2005 ዓ,ም ከቦታዉ መነሳቱ በወቅቱ ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማዋ ነዋሪዎች ሐዉልቱ የተመለሰበትን ታሪካዊ ቦታ ለማየት አሁንም ወደ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ እየሄዱ እንደሆነ ተሰምቶአል። ሐዉልቱ ወደ ነበረበት ቦታ መመለሱን አስመልክቶ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን አንዳንዶቹን በማነጋገር ዘገባ አዘጋጅቶልናል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ