የአሸባብ ጥቃት ስጋት በመቅዲሾ
ረቡዕ፣ መስከረም 24 2004ማስታወቂያ
የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ፕሬዝዳንት ሼክ ሸሪፍ ሼክ አህመድ በሶማሊያ የ3 ቀናት ሃዘን አውጀዋል ። ፕሬዝዳንቱ መዲናይቱን ወደፊት ሊያጋጥሙ ከሚችሉ የቦምብ ጥቃቶች ለመጠበቅ አስፈላጊው የፀጥታ ጥበቃ እርምጃ እንደሚወሰድም ቃል ገብተዋል ። ለትናንቱ ጥቃት ሃላፊነቱን የወሰደው አሸባብ ደግሞ ጥቃቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል ። ስለ መቅዲሾ ጊዜያዊ ሁኔታ ሂሩት መለሰ የየዶቼቬለ የመቅዲሾ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሁሴን አዌይስ አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች ።
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ