የአሸባሪዎች ጥቃት ሰባተኛ አመት መታሰቢያ
ሐሙስ፣ መስከረም 1 2001ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ በአሸባሪዎች የተጠቃችበት ሰባተኛ አመት ዛሬ በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ነዉ።አሸባሪዎቹ ከጠለፏቸዉ አዉሮፕላኖች የመጀመሪያዉ ከWorld Trade Center መንታ-ሕንፃዎች ካአንዱ ጋር የተላተመበት ሰአት በፀጥታ ታስቧል።አደጋዉን እንደ ሐገር መሪ ለመጨረሻ ጊዜ የሚያስቡት ፕሬዝዳት ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽ መከላከያ ሚንስቴር በተደረገዉ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።ቡሽን ለመተካት የሚፎካከሩት ሴናተር ባራክ ኦባማና ሴናተር ጆን መከይን በኒዮርኩ ሥነ-ሥርዓት ላይ እየተካፈሉ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ።