1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአስዋን ግድብ

ዓርብ፣ ኅዳር 22 2010

ታሪካዊው እና ትልቁ የአስዋን ግድብ በአካባቢው ነዋሪዎች እና በሥነ ምህዳሩ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሯል። ለምዕተ ዓመታት ለአካባቢው መሬት እንደ ማዳበሪያ ያገለግል የነበረው የናይል ውሐ ደለል መጠን መቀነስ ገበሬው ፊቱን ወደ ማዳበሪያ እንዲያዞር አድርጎታል።

https://p.dw.com/p/2ocT0
Assuan-Staudamm in Ägypten
ምስል imago/Harald Lange

የአስዋን ግድብ እና ተጽእኖዎቹ

ለተለያየ አገልግሎት የሚሰሩ የወሐ ግድቦች ጠቀሜታ ከፍተኛ ቢሆንም አንዳንዴ ከባድ ሊባል የሚችል ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ። በዚህ ረገድ የግብጹ የአስዋን ግድብ ተጠቃሽ መሆኑን አና ኦስዩስ ከካይሮ የላከችው ዘገባ ያስረዳል። እንደዘገባው ታሪካዊው እና ትልቁ የአስዋን ግድብ በአካባቢው ነዋሪዎች እና በሥነ ምህዳሩ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሯል። ለምዕተ ዓመታት ለአካባቢው መሬት እንደ ማዳበሪያ ያገለግል የነበረው የናይል ውሐ ደለል መጠን መቀነስ ገበሬው ፊቱን ወደ ማዳበሪያ እንዲያዞር አድርጎታል። ይህም የአፈሩ የጥራት ደረጃ እየቀነሰ እንዲሄድ ማድረጉ ተገልጿል። ዘገባውን ያጠናቀረው እንዳልካቸው ፈቃደ ዝርዝሩን ያቀርብልናል።  
እንዳልካቸው ፈቃደ 
ኂሩት መለሰ