የአስናቀች ወርቁ ዜና እረፍት5 መስከረም 2004ዓርብ፣ መስከረም 5 2004የሁለገብዋ አርቲስት የአስናቀች ወርቁ የቀብር ስነስርዓት በርካታ የኪነጥበብ ባለሞያዎች እና አድናቂዎቿ በተገኙበት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ተፈፀመ ።https://p.dw.com/p/RmFPምስል Paul Krenzማስታወቂያወደ ግማሽ ምዕተ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ የመድረክ እንቁ ሆና የዘለቀችው አስናቀች ወርቁ በክራር አገራረፏ እና በትወና ችሎታዋ በሙያ ባልደረቦችዋና እና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት የሚቸራት የኪነጥበብ ባለሞያ ነበረች ። የህይወት ታሪኳን የፃፉትን አርቲስት ጌታቸው ደባልቄን ስለ አስናቀች ጠይቀናል ። ሂሩት መለሰ ተክሌ የኋላ