የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና የአዉሮጳ ሕብረት
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 8 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት የደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የዴሞክራሲ መርሆችንና የዜጎችን መብት ሊጥስ እንደሚችል የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ አስታወቁ።የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ ወይዘሮ ፌዴሪካ ሞግሆሪኒ ለኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ለአቶ ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ስልክ ደዉለዉ አዋጁ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ ያሳሰባቸዉ መሆኑን ገልፀዋል።የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ግን መንግሥታቸዉ የደነገገዉ አዋጅ መሠረታዊ መብቶችን አይጥስም ብለዉ መናገራቸዉን ሕብረቱ አስታዉቋል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለስ