የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሥጋት
ሰኞ፣ ጥቅምት 7 2009ማስታወቂያ
ባለፈው ቅዳሜ ይፋ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የቀይ ዞን በመመስረት የሰዓት እላፊ ገደብ ጥሏል። ማስፈጸሚያ መመሪያውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒሥትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ እንደገለጡት «በአገሪቱ በሁሉም አቅጣጫዎች ባሉ ድንበሮች 50 ኪ.ሜ. ወደ ውስጥ ገባ ብሎ» የሚገኙ አካባቢዎች፤ ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች በሚያመሩ ዘጠኝ መንገዶች ግራና ቀኝ በ25 ኪ.ሜትር ርቀት የቀይ ዞን መመሥረቱን አስታውቀዋል። በቀይ ዞን ውስጥ ከተካተቱት መካከል «የኢኮኖሚ አውታሮች፣ መሰረት ልማትና የኢንቨስትመንት ተቋማት፣ የእርሻ ልማቶች፣ ፋብሪካዎች» ይገኙበታል። መመሪያው በእነዚህ አካባቢዎች ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር ከቀኑ 12 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰአት ድረስ ማንኛውም ሌላ ሰው እንዳይንቀሳቀስ ከልክሏል።የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር ያነጋገራቸው የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት «ህግን አገናዝቦ ያልወጣ» ያሉት አዋጅ እንዲሻር ጥሪ አቅርበዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ
ሒሩት መለሰ