1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው መሰናበት

ሐሙስ፣ ጥር 29 2006

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከ31 ዓመት በኃላ ለአፍሪቃ ዋንጫ ተሳትፎ ያበቁ አሰልጣኝ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው። ይሁንና ትናንት የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውን ከነበራቸው ኃላፊነት ማንሳቱን አሳውቋል።

https://p.dw.com/p/1B3vH
Afrika-Cup Äthiopien
ምስል DW/H. Turuneh

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት ጁነዲን በሻህ ለሮይተርስ አሰልጣኝ ሰዉነት እና ምክትላቸዉ እንዲሁም የበረኛዉ አሰልጣኝ ብሄራዊ ቡድኑን ባለፉት ዓመታት አነቃቅተዉ ለታሪካዊ ስኬት ማድረሳቸዉን ገልጸዋል። ሆኖም አሁን የተጣለዉ መሠረት የተሻለ ፍሬ እንዲያሳይ በወጣቶች መገንባት ይኖርበታል ብሎ ፌዴሬሽኑ እንደሚያምን እና፤ በቅርቡም አዲስ አሰልጣኝ እንደሚሰየም አመልክተዋል። አዲሱ አሰልጣኝ ከሀገር ዉስም ሆነ ከዉጭ ሊሆን እንደሚችል ነዉ የተገመተዉ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ እንደሚሉት ፌሬዴሽኑ ያሳለፈዉን ዉሳኔ አልጠበቁትም። አቶ ሰውነትን በስልክ አነጋግረናቸዋል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ