የአርያና ግራንዲ ዝግጅት
ሰኞ፣ ግንቦት 28 2009ማስታወቂያ
የብሪታንያ ፖሊስ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ሰባት ሰዎች በተገደሉበት እና 48 ሰዎች ከቆሰሉበት ከለንደን ብሪጁ ጥቃት ጋር ግንኙነት አላቸው ብሎ የጠረጠራቸውን ማደን እና ማሰሩን ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። የታሰሩት ቁጥር 12 ደርሷል። በብሪታንያ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ለተፈፀመው ለዚሁ ጥቃት ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ቡድን ሃላፊነቱን ወስዷል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎች ማደኑን በቀጠለበት በትናንትናው እለት በብሪታንያዋ ሰሜናዊ ከተማ ማንቼስተር ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው የአርያና ግራንዲ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በተጣለው ጥቃት ለሞቱት እና ለተጎዱ ቤተሰቦች መርጃ የተዘጋጀው የሙዚቃ ትርዒት ተካሂዷል። የ23 ዓመትዋ ወጣት አርያና በማንቼስተር ከተማ ባዘጋጀችው በዚሁ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ሌሎች እውቅ ከያንያንም ተካፍለዋል። የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳው ጉጌታነህ ዝዝርሩን ልኮልናል ።
ድልነሳው ጉታነህ
ኂሩት መለሠ
ሸዋዬ ለገሠ