1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአርትዩር ራምቦ መጽሐፍ በአማርኛ

ሐሙስ፣ ሰኔ 16 2008

ከ 19 ነኛው ክፍለ ዘመን ታዋቂ የዓለማችን ጸሀፍት አንዱ እንደነበር የሚነገርለት ፈረንሳዊው ባለቅኔ አርትዩር ረምቦ የሥነ-ፅሁፍ ሥራዎች ደራሲው በተለይ ከኢትዮጵያዋ ከሐረር ከተማ ጋር የነበረውን ቁርኝነት ያሳያሉ።

https://p.dw.com/p/1JC6B
Arthur Rimbaud
ምስል BNF, Estampes

[No title]

ረምቦ ሐረር ውስጥ በቆየባቸው አሥር በሚጠጉ ዓመታት ውስጥም የአፄ ምኒልክ አማካሪ ከነበረው ከስዊዛዊው አልፍሬድ ኤልግ እና ከራስ መኮንን ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንደነበረው ይወሳል። በ37 ዓመቱ ሕይወቱ ያለፈው የረምቦ የትውልድ ከተማ ሻርቪል ከሐረር ጋር በእህትማማችነት የተቆራኘች ከተማ ናት። ሐረርም የረምቦን የቀድሞ መኖሪያ ቤተ መዘክር አድርጋለች። የአርተር ራረምቦ የሥነ-ጽሁፍ ሥራዎች በበርካታ ቋንቋዎች የተተረጎሙ ቢሆንም ወደ ኣማርኛ የተመለሱት ግን በቅርቡ ነው። የዚህ እውቅ ፈረንሳዊ ደራሲ በርካታ የግጥምና የሥነ-ጽሁፍ ስብስቦች የተካተቱበት ከፈረንሳይኛ ቋንቋ ወደ አማርኛ የተተረጎመ መጽሐፍ ፓሪስ ውስጥ ባለፈው ሰሞን ተመርቋል። በምረቃው ሥነ-ስርዓት ላይ የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ተገኝታ ነበር።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ