የ4 የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መግለጫ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 17 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙ አራት የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ያወጡትን መግለጫ አሰራጭተዋል። ፓርቲዎቹ በሦስት አበይት ጉዳዮች ላይ ያተኮረው ቅራኔያቸውን የገለጡ ሲኾን፤ በተለይ በሶማሌ እና በኦሮሚያ መስተዳድሮች ድንበር አካባቢ ስላለው ኹኔታ ትኩረት አድርገዋል። በአዋሳኝ ግዛቶች ለሚከሰቱ ግጭቶች ተጠያቂዎቹ ህዝቡ ሳይሆን አመራሮች ናቸው ተብሎ ቢነገርም እስካሁን ርምጃ አለመወሰዱ ቅር እንዳሰኛቸውም ገልጠዋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ