1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአረንጓዴ ጀግኖች

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 8 2000

ጀግንነት በየመስኩ በተለመደባት ምድር ለተፈጥሮና ለአካባቢ ባደረጉት ክብካቤ አስተዋፅዖዋቸዉ እዉቅና ያገኘ ወገኖች ሽልማት ማግኘት ከጀመሩ ጥቂት ዓመታት ተቆጠሩ።

https://p.dw.com/p/Ed3Q
ፕሬዝደንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ
ፕሬዝደንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስምስል picture-alliance/ dpa

በአገራችን ባለፈዉ ሰሞን የአካባቢ ተቆርቋሪዎች መድረክ ያስተባበረዉ የአረንጓዴ ጀግኖች ሽልማት ተካሂዷል። ዝግጅት የታሰበዉ በ1997ዓ,ም ሲሆን በቀጣዩ ዓመት በ1998 የመጀመሪያዉ፤ ዓምና ደግሞ ሁለተኛዉ እያለ ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ ነዉ የአረንጓዴ ጀግኖች በሚል ሽልማቱ የተሰጠዉ። የተሸላማዊቹ ዋና ሃብት ዕዉቅና ማግኘታቸዉ ሲሆን ከምንም በላይ ሰዉ በለፋዉና ባደረገዉ አስተዋፅዖ መታወሱ እሱን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ያበረታታልና ይበል የሚባል ጅምር ነዉ።