የአሜሪካ የፊናንስ ቀውስ፤ መንስዔው፤ መዘዙ
ረቡዕ፣ መስከረም 21 2001ማስታወቂያ
በዚህ በአውሮፓም የሰሞኑ ዓቢይ ወሬ ይሄው የፊናንሱ ገበያ ችግር ሆኗል፤ የኤኮኖሚ ቀውስ ይከተላል-አይከተልም ብዙዎችን በስጋት የጠመደው ጉዳይ ነው። የቀውሱ መንስዔ ምንድነው፤ አዝማሚያ ሂደቱስ? የ 30ኛዎቹ ዓመታት የዓለም ኤኮኖሚ ቀውስ በር እያንኳኳ ነው ለማለት ይቻላል ወይ? በነዚህና ቀውሱ በታዳጊው ዓለም ልማት ላይ ሊኖረው በሚችለው ተጽዕኖ ኢትዮጵያዊው የምጣኔ-ሐብት ባለሙያ ዶር/ በፈቃዱ ደገፌ!