የአሜሪካ የሎተሪ ቪዛና ክስ
ዓርብ፣ ሰኔ 17 2003ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካ መግባትና መስራት የሚያስችለዉን የዘንድሮዉን የሎተሪ ቪዛ በመሠረዙ ተከሠሠ።ክሱን የመሠረተዉ ሗይት ኤንድ አሶሽየትስ የተሰኘዉ የጥብቅና ተቋም እንደሚለዉ የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት የእድለኞችን ዉጤት መሠረዙ የአሜሪካንን ቃል የመጠበቅ መርሕ የሚጥስ ነዉ።የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በዘንድሮዉ ሎተሪ እጣ የወጣላቸዉን የሃያ-ሁለት ሺሕ ሰዎች ዉጤት ሠርዟል።መስሪያ ቤቱ ዉጤቱን ለመሠረዙ የሰጠዉ ምክንያት ዕጣ አዉጪዉ ኮምፒዉተር ተበላሽቷል የሚል ነዉ።
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ
ሂሩት መለሠ