አሜሪካ እና እስራኤል
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 21 2009ማስታወቂያ
የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት እስራኤል ምሥራቅ እየሩሳሌም እና በዮርዳኖስ ወንዝ ምዕራባዊ ዳርቻ የምታካሂደው የሰፈራ ግንባታ ህገ ወጥ ነው ሲል ባለፈው ሳምንት ውሳኔ ካሳለፈ ወዲህ እሥራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ እየተወዛገቡ ነው ። ዩናይትድ ስቴትስ ድምፅ ን በድምጽ የመሻር መብትዋን ተጠቅማ ውሳኔው እንዳያልፍ አለማድረጓ እስራኤልን አስቆጥቷታል ። አንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ደግሞ ውሳኔውን እናስቀለብሳለን እያሉ ነው ። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በበኩላቸው የእስራኤልን አቋም መደገፍ የአሜሪካንንም ሆነ የእሥራኤልን እሴቶች እንደመቃረን የሚቆጠር ነው ብለዋል ። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል ።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ