1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ

ረቡዕ፣ ግንቦት 6 2006

በኢትዮጵያ የፖለቲካው መድረክ እንዲሰፋና የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር ግፊት ማድረግ እንደምትቀጥል አሜሪካን አስታወቀች ። ኢትዮጵያና ግብፅ በአባይ ላይ ያላቸውን ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱም ጠየቀች ።

https://p.dw.com/p/1Bzpw
ምስል AP

የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በኢትዮጵያ የፖለቲካው መድረክ እንዲሰፋና የፕሬስ ነፃነት እንዲከበር መንግሥታቸው ግፊት ማድረጉን እንደሚቀጥል አስታወቁ ። ምክትል ሚኒስትሯ ዛሬ በቪድዮና በድረ ገፅ ቀጥታ ስርጭት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች በሰጡት መልስ ኢትዮጵያና ግብፅ በአባይ ላይ ያላቸውን ልዩነቶቻቸውን በውይይት እንዲፈቱም ጠይቀዋል ። የደቡብ ሱዳን መንግሥትና መንግሥት የሚወጉት ኃይሎች የራሳቸውንጥቅም ወደ ጎን በመተው ሰላም ለማውረድ እንዲጥሩም ጥሪ አስተላልፈዋል ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ