የአሜሪካ ምርጫና ተቃዉሞ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 5 2008ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የሚያደርጉት የምረጡኝ ዘመቻ የአብዛኛዉን አሜሪካዊ ትኩረት በሳበበት ባሁኑ ወቅት የሐገሪቱን የምርጫ ሒደትና የሐብታም ድርጅቶችን ጣልቃገብነት የሚቃወሙ አሜሪካዉያን ላደባባይ ሠልፍ እየታደሙ ነዉ።እራሳቸዉን የዴሞክራሲ ንቅናቄ ብለዉ የሚጠሩት ወገኖች የአሜሪካ ምርጫ እና ፖለቲካ በቱጃር ኩባንያ፤ ድርጅቶች፤ ተቋማትና ግለሠቦች መነዳቱ እንዲቆም ጠይቀዋል።በቅርቡ ርዕሠ-ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ተጋጭተዉም ነበር።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ የላከልን ዘገባ አለ።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ