1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን ፊልም እና የሙስሊሞች ተቃዉሞ

ሐሙስ፣ መስከረም 3 2005

ነብዩ መሐመድን የሚያንቋሽሸዉ የአሜሪካ ፊልም መሠራጨቱ ያስቆጣዉ ሙስሊም አሜሪካን መቃወሙን እንደቀጠለ ነዉ።ትናንት ካይሮ፥ ቱኒስ፥ ራባትና ካርቱም አደባባዮች የወጣዉ ሕዝብ የአሜሪካ ኤምባሲዎችን ከብቦ የአሜሪካን ባንዲራ እያቃጠለ አሜሪካን ሲያወግዝ ነዉ የዋለዉ።

https://p.dw.com/p/1686P
የአሜሪካን ፊልም እና የሙስሊሞችተቃዉሞዉምስል Reuters

ነብዩ መሐመድን የሚያንቋሽሸዉ የአሜሪካ ፊልም መሠራጨቱ ያስቆጣዉ ሙስሊም አሜሪካን መቃወሙን እንደቀጠለ ነዉ።ትናንት ካይሮ፥ ቱኒስ፥ ራባትና ካርቱም አደባባዮች የወጣዉ ሕዝብ የአሜሪካ ኤምባሲዎችን ከብቦ የአሜሪካን ባንዲራ እያቃጠለ አሜሪካን ሲያወግዝ ነዉ የዋለዉ።በተለይ ካይሮና ቱኒስ አደባባይ የወጣዉ ሕዝብ ወደ የአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢዎች ገብቶ አደጋ ለመጣል ሲሞክር በፖሊስ ሐይል ታግዷል።ዛሬ ብራስልስ ዉስጥ የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት ማኑኤል ባሮሶን ጨምሮ የሕብረቱን ባለሥልጣናት ያነጋገሩት የግብፁ ፕሬዝዳት መሐመድ ሙርሲይ በበኩላቸዉ አወዛጋቢዉን ፊልም የሠሩና ያሰራጩትን ወገኖች አዉግዘዋል።«ይሕ ነብያችንን የሚያንቋሽሸዉ ፊልም ግብፅ ዉስጥና በመላዉ የዓረብ ዓለም ታላቅ ቁጣን ቀስቅሷል።እንዲሕ አይነቱን ጠብ አጫሪነትና ጥላቻን በዓለም የሚነዙ ወገኖችን አጥብቀን እንቃወማለን።»ፕሬዝዳት ሙርሲያ በአሜሪካ የግብፅ ኤምባሲ ፊልሙን የሰሩና ያሰራጩ ወገኖችን እንዲከስ ማዘዛቸዉም ተዘግቧል።ፕሬዝዳንቱ የዚያኑ ያክል ፊልሙን በመቃወም አደባባይ የወጣዉ ሕዝብ ሰዉና ንብረትን ከመተናኮል እንዲታቀብ አደራ ብለዋል። ዛሬ የቴሕራን-ኢራንና የሠነዓ-የመን ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተዉ አሜሪካን ሲያወግዙ ነዉ የዋሉት።አንድ የኢራቅ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን በበኩሉ ኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጥቅሞችን ለማጥቃት ዝቷል።ፊልሙ ሕዝባዊ ቁጣና ረብሻ ይቀሰቅሳል ብሎ የፈራዉ የአፍቃኒስታን መንግሥት ደግሞ ፊልሙን የሚያሰራጨዉን ዩ-ቱዩብ የተሰኘዉን አምደ መረብ ዘግቷል።

ነብዩ ሲራክ

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ