1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን ጦር ከኢራቅ መውጣት ያሳደረው ስጋት

ዓርብ፣ ነሐሴ 14 2002

ከሰባት ዓመት በላይ ኢራቅ ከቆዩት የአሜሪካ ተዋጊ ጦር ኃይል አባላት የመጨረሻዎቹ ትናንት ኢራቅን ለቀው ወጥተዋል ። የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢራቅ ጦርነት ማብቃቱን ትናንት በይፋ አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/OslS
ምስል AP

በርካታ ኢራቃውያን የአሜሪካን ጦር ሀገራቸውን ለቆ በመውጣቱ የተቀላቀለ ስሜት ነው ያደረባቸው ። በአንድ በኩል ሀገሪቱን በኃይል የያዘው የአሜሪካን ጦር በመውጣቱ ደስተኞች ናቸው ። በሌላም በኩል የፀጥታው ሁኔታ ከቀድሞው እጅግ ይባባሳል ብለው መስጋታቸውም አልቀረም ። የዶይቼቬለው ራይነር ዞሊሽ እንደሚለው የአሜሪካን ሠራዊት ኢራቅን ለቆ ከወጣ በኃላ የኢራቅ ፀጥታ ተረጋግቶ መቀጠሉ ለብዙዎች ኢራቃውያን አስተማማኝ አይደለም ።
ራይነር ዞሊሽ ፣ ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ሂሩት መለሰ