የአሜሪካን የገንዘብ ድጋፍ እና አፍሪቃ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 17 2009ማስታወቂያ
ትራምፕ በአቋማቸዉ ከቀጠሉ የአፍሪቃ ሃገራት በተለይም ኢትዮጵያ፣ ናይጀሪያ፣ ጋና፣ ኮት ዴቩዋር፤ ደቡብ አፍሪቃ፣ አንጎላ እና ሌሎችም ሃገራት በጣም ይጎዳሉ፣ የምጣኔ ሃብታቸዉም ለአደጋ ይጋለጣል። ለዶቼ ቬለ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡ አንድ የኤኮኖሚ ባለሙያ በተለይ ከአፍሪቃ ሃገራት ከፍተኛዉን የገንዘብ ድጋፍ የምታገኘዉ ኢትዮጵያ ተጎጂ እንደምትሆን አመልክተዋል። ሌሎቹ የአፍሪቃ ሃገራት ከፍተኛ የማዕድን ሽያጭ የሚያደርጉ ሲሆን ኢትዮጵያ ግን 3,5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በማግኘት በፀረ ሽብር ዘመቻዉ የበለጠ የአሜሪካን አጋር ብትሆንም የእርዳታዉ ቀጣይነት አይታያቸዉም ምሁሩ። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ