1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን ና የሶማሊያ ግንኙነት

ሐሙስ፣ ጥር 9 2005

«ዩናይትድ ስቴትስ በግልፅ ባታሳውቅም መንግሥቱን ትደግፍ ነበር ። ሆኖም እንደኔ ዩናይትድ ስቴትስ የሶማሊያን መንግሥት በህጋዊ መንግሥትነት በይፋ ስትቀበልና ይሁንታዋን ስትገልፅ ግን የመጀመሪያዋ ነው ።» አንድሪውስ አታ አሳሞዋ ደቡብ አፍሪቃ ፕሪቶሪያ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የፀጥታ ጥናት ተቋም ከፍተኛ አጥኚ

https://p.dw.com/p/17MPO
Residents walk past the campaign billboard of Somalia's presidential candidate Hassan Sheikh Mohamud in Somalia's capital Mogadishu, September 9, 2012. Somalia's lawmakers voted overwhelmingly on Monday for Mohamud as the country's next president, with the streets of the capital erupting into celebratory gunfire, Reuters witnesses said. Two of the four candidates who made it to the second round of voting opted out, leaving the incumbent President Sheikh Sharif Ahmed and Mohamud.Picture taken September 9, 2012. REUTERS/Feisal Omar (SOMALIA - Tags: POLITICS ELECTIONS)
ምስል picture-alliance/dpa

ዩናይትድ ስቴትስ ለአዲሱ የሶማሊያ መንግሥት ዛሬ እውቅና እንደምትሰጥ አስታወቃለች ። የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ መሕመድ ዛሬ ማምሻውን የዲፕሎማሲያዊ እውቅና ማረጋገጫውን ሰነድ ዋሽንግተን ውስጥ ይለዋወጣሉ ። አሜሪካን ከ20 አመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሶማሊያ መንግሥት እውቅና መስጠቷ ለአዲሱ የሶማሊያ መንግሥት ና ለሃገሪቱም መፃኤ እድል ጠቃሚ መሆኑን ፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪቃ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የፀጥታ ጥናት ተቋም ጉዳዮች አጥኚ አንድሪውስ አታ አሳሞዋ አስታውቀዋል ።
አሜሪክና ለሶማሊያ እውቅና መስጠቷ  ። አሜሪካንን በመጎብኘት ላይ ያሉት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ መሕሙድ ዛሬ ማምሻውን በሚካሄድ ስነ ስርዓት ከዩናይትድ ስቴትስዋ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተን ጋር የእውቅና ማረጋገጫውን ዲፕሎማሲያዊ ሰነድ ሲለዋወጡ አሜሪካን ለሶማሊያ የምትስጠው እውቅ ይፋ ይሆናል ። እጎአ ከ1991 አንስቶ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት የሌላት ሶማሊያ ከአሜሪካን ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረቷ በሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ ከፋች ና እንድ ትልቅ እርምጃም ተደርጎ ተወስዷል ። እጎአ በ1993 የሶማሊያ ሚሊሽያዎች 2 የአሜሪካን ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችን መትው ከጣሉና 18 የአሜሪካን ወታደሮች ተገድለው 18 ከቆሰሉ ወዲህ አንድም የአሜሪካን ወታደር ወደ ሶማሊያ ዝር ብሎ አያውቅም ። ሆኖም ባለፈው መስከረም አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት በምርጫ ሥልጣን ሲይዙ የዋሽንግተን አስተዳደር ምርጫውን ደግፎ ሲያወድስ  ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሊንተንም የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላልፈው ነበር ። ፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪቃ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የፀጥታ ጥናት ተቋም ከፍተኛ አጥኚ አንድሪውስ አታ አሳሞዋ እንዳሉት ዩናይትድ ስቴትስ አሁን ለሶማሊያ በይፍ እውቅና ብትሰጥም ከዚያ አስቀድሞም ቢሆን ሶማሊያን ትደግፍ ነበር
« ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ መንግሥት ምሥረታ ሂደት ውስጥ የነበራት ተሳትፎ ምርጫውና በአጠቃላዩ ሂደትም የሽግግር መንግሥቱ ለፍፃሜ እንዲበቃ አድርጓል ። በርግጥ ዩናይትድ ስቴትስ በግልፅ ባታሳውቅም መንግሥቱን ትደግፍ ነበር ። ሆኖም እንደኔ ዩናይትድ ስቴትስ የሶማሊያን መንግሥት በህጋዊ መንግሥትነት በይፋ ስትቀበልና ይሁንታዋን ስትገልፅ ግን የመጀመሪያዋ ነው ። ከዚያድ በሬ መንግሥት ውድቀት በኋላም ሆነ ከዛ ቀጥሎ የተቋቋሙት መንግሥታት ፣ የሽግግር መንግሥታት ወይም ደግሞ አብሮ ለመሥራት አሰቸጋሪ የሆኑ መንግሥታት ነበሩ ።»
እውቅናው ቢዘገይም ለመንግሥትም ይላሉ አሳሞዋ በአሁኑ ሰአት መሰጠቱ ለሃገሪቱም ሆነ ለህዝቡ ከብዙ አቅጣጫ በርካታ ጥቅሞች አሉት ።

Residents walk past the campaign billboard of Somalia's presidential candidate Hassan Sheikh Mohamud in Somalia's capital Mogadishu, September 9, 2012. Somalia's lawmakers voted overwhelmingly on Monday for Mohamud as the country's next president, with the streets of the capital erupting into celebratory gunfire, Reuters witnesses said. Two of the four candidates who made it to the second round of voting opted out, leaving the incumbent President Sheikh Sharif Ahmed and Mohamud.Picture taken September 9, 2012. REUTERS/Feisal Omar (SOMALIA - Tags: POLITICS ELECTIONS)
ምስል picture-alliance/dpa
FILE - In this Wednesday, Dec. 14, 2011 file photo, two Kenyan army soldiers shield themselves from the downdraft of a Kenyan air force helicopter as it flies away from their base near the seaside town of Bur Garbo, Somalia. Kenya's military said Friday, Sept. 28, 2012 that its troops attacked Kismayo, the last remaining port city held by al-Qaida-linked al-Shabab insurgents in Somalia, during an overnight attack involving a beach landing. (Foto:Ben Curtis, File/AP/dapd).
ምስል AP

« እውቅና መስጠቱ  በራሱ፣ በአዲሱ አመራር ላይ አዲስ ጥቅምን የማስጠበቅና ተስፋን የሚያሳድር መንፈስ የመኖሩን ሃቅ ይናገራል ። አዲሱ አመራር ወደ ሥልጣን እንደመጣ አንዳንድ በሶማሊያ ጉዳይ እጃቸውን ያስገቡ ሃገሮች ፣ ከዚህ ቀደም በሶማሊያ የተቋቋሙ አዳዲስ መንግሥታት ከሚጋፈጧቸው ፈታኝ ሁኔታዎች በመነሳት ፣ በአዲሱ መንግሥት ሁኔታዎች ወዴት አቅጣጫ ሊያመሩ እንደሚችሉ ስጋት ነበራቸው ። ዕውቅናው ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መምጣቱ ሌሎች በሶማሊያ ጉዳይ እጃቸውን ያስገቡ ሃገሮች በአዲሱ አመራርና በሶማሊያ ላይ ያላቸው ተስፋ እንዲለመልም ማድረግ ይጀምራል ማለት ነው ።

--- 2012_10_01_somalia_galkayo.psd

ይህ ደግሞ የሶማሊያ ህዝብ ራሱ በአዲሱ አመራር ላይ ያለው ፍላጎት እንዲታደስም ያደርጋል ።  ለአዲሱ አመራር ጥሩ ነው ። ምክንያቱም ይህ ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችላቸው ተቀባይነት የማግኘት ስሜት ያሳድርባቸዋል ። ሃገሪቱን የሚመሩም የሶማሊያን ምጣኔ ሐብትና መፃኤ እድል ለማፅናት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረቷ ጥሩ አጋጣሚ ነው ። »
የዩናይትድ ስቴትስና የሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመሰርቱ እጅግ ጠቃሚ ነው የሚሉት ኦሳማዋ ግንኙነቱ ግን በጥንቃቄ ካልተያዘ የአክራሪዎች መጠቀሚያ መሳሪያ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አላቸው
በሃገር ውስጥ ባሉት በርካታ ፈታኝ ሁኔታዎች ምክንያት አዲሱ መንግሥት የአክራሪ ሙስሊሞች መዘባበቻ እንዳይሆን ጉዳዩ በጥንቃቄ መያዝ አለበት ። ምናልባት አዲሱ መንግሥት የምዕራቡ አለም በተለይም የዩናይትድ ስቴትስ አሻንጉሊት ነው እያሉ እንዳይወቅሱት ማለት ነው ። ስለዚህ ለዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ ጉዳይ በቀጥታ ለመሳተፍ ጥሩ አጋጣሚ ነው ። ዩናይትድ ስቴትስ ከአዲሱ መንግሥት ጋር የሚኖራት ግንኙነት የአሸባብ አጀንዳ እንዳይሆን በጥንቃቄ መያዝ ይኖርበታል ። »
በኦሶማዋ እምነት የአሜሪካንና የሶማሊያ መሪዎች ቅርርብ የበላይ ና የበታች ሊሆን አይገባም ። ይህ ከሆነ ግን አክራሪዎች ግንኙነቱን  ለአፍራሽ ፕሮፖጋንዳ መሳሪያነት ሊጠቀሙበትና ለራሳቸውም ድጋፍ ሊያሰባስቡበት ይሞክራሉ 

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ