የአሜሪካን ምክር ቤት እና የ CIA ውዝግብ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 8 2001ማስታወቂያ
CIA የአልቄይዳ መሪዎችን ለመግደል የሚሰማሩ ቡድኖችን ለማቋቋም ያቀደውን አሁን ግን የተቋረጠውን ምስጢራዊ መርሀ ግብር ማሳወቅ ሲገባው በዲክ ቼኒ ቀጥተኛ ትዕዛዝ መደበቁ ከፍተኛ የህግ ጥሰት መሆኑ ተጠቁሟል ። በሌላ በኩል የፍትህ ሚኒስቴር የቀድሞውን የአሜሪካን ፕሬዝዳንት የጆርጅ ቡሽን አስተዳደር የቁም ስቅልና የእንግልት መርሀ ግብር ለክስ ሊያቀርብ እንደሚችልም እየተነገረ ነው ። ዝርዝሩን አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ፣ሸዋዬ ለገሠ