1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን መንግሥት መግለጫ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 3 2009

የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት ትናንት ማምሻውን በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቃባይ ጆን ኪርቢ በኩል ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ የደነገገችው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያስከትል የሚችለው ተጽእኖ እንደሚያሳስበው ገልጿል፡፡

https://p.dw.com/p/2RCbn
USA Flagge auf Halbmast in Baton Rouge
ምስል Reuters/J. Penney

US statement on Ethiopia's state of Emergency - MP3-Stereo

የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት ትናንት ማምሻውን በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቃባይ ጆን ኪርቢ በኩል ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ የደነገገችው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያስከትል የሚችለው ተጽእኖ እንደሚያሳስበው ገልጿል፡፡ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰውን ማሰር፣ የመገናኛ ዘዴዎችን እና የኢንተርኔት አገልግሎትን ማገድን ጨምሮ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ላይ የሚደረግ ተጨማሪ እቀባ፣ የህዝባዊ ስብሰባዎች ክልከላ እና የሰዓት ዕላፊ ገደብ በቃል አቀባዩ በኩል ከተጠቀሱ አሳሳቢ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ተስፋለም ወልደየስ

ነጋሽ መሐመድ