1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማዕቱ ግብና ኢትዮዽያ

ሰኞ፣ መስከረም 10 2003

ኢትዮዽያ በአማዕቱ ግብ አንጻር ምን ላይ እንደደረሰች የሚያሳይ ውይይት ተካሄደ። በአንዳንድ ዘርፎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እንዳሳየች ተመለከተ።

https://p.dw.com/p/PHhF
ምስል AP

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የአማዕቱ ግብ በሚል በነደፈው እቅድ መሰረት የኢትዮዽያን ሁኔታ የተመለከተ ውይይት ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተጠሪዎች ጋር በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በመልማት ላይ ያሉ ሀገራት ድህነትን በማስወገድ ረገድ መሪ እቅድ በማውጣት የነደፈው ስልት እንደ ጎሮጎርሳውያን አቆጣጠር እስከ 2015 በስራ ይተረጎማል የሚል እምነት አለው። አምስት አመት ብቻ የቀረው የአማዕቱን ግብ በተመለከተ ኢትዮዽያ የት ነው ያለችው? በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የተካሄደው ውይይት የኢትዮዽያን ደረጃ የፈተሸ ነበረ። ውይይቱን የተከታተለው ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ አድርሶናል።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ