የአልሸባብ ግስጋሴና የኢትዮዽያ ምላሽ
ሐሙስ፣ ግንቦት 5 2002ማስታወቂያ
ኤልበርዴ ከኢትዮዽያ ድንበር ብዙም የማትርቅ የሰሜን ሶማሊያ ከተማ ናት። ሮይተርስ የአልሸባብ የጦር አዛዥን ጠቅሶ እንደዘገበው በኤልበርዴ የመንግስቱ ጦር የለም። አዛዡ ሼክ ሀሰን ሞ አሊም ታኮው እንደገለጹት አልሸባብ በከባድ መሳሪያ ከደበደባት ኤልበርዴ የመንግስቱ ጦር ብዙም አልቆየም። ወደ ኢትዮዽያ ድንበር ዘልቀው ገብተዋል ። የኤልበርዴን መያዝ የኢትዮዽያ መንግስት ተራ ፕሮፖጋንዳ ሲል አጣጥሎታል። የኮሚኒኬሽንስ ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል አልሸባብን ለማግዘፍ ተብሎ የተፈበረከ ወሬ ብለውታል።
መሳይ መኮንን
ሂሩት መለሰ