አል ሲሲ እና የመብት ተሟጋቾች ተቃውሞ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 15 2010ማስታወቂያ
ፈረንሳይን በመጎብኘት ላይ ያሉት የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አምነስቲ ኢንተርናሽናልንን እና ሂዩመን ራይትስ ዋች ከመሳሰሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። እነዚህ የመብት ተሟጋች ተቋማት የአል ሲሲ መንግሥት ጋዜጠኞችን፣የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እንዲሁም ግለሰቦችን ከማሰር ባለፈ ቁም ስቅል ይፈጽምባቸዋል ሲሉ ይወቅሳሉ። የፈረንሳይ መንግሥትም ከአልሲሲ ጋር ምንም ዓይነት ኤኮኖሚያዊም ሆነ ወታደራዊ ስምምነት እንዳያደርግም ጠይቀዋል። የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮም ግብጽ ለራስዋ ስትል ሰብዓዊ መብቶችን እንድትጠብቅ ጠይቀዋል። አል ሲሲ ግን ከመብት ተሟጋቾች የሚቀርቡባቸውን ክሶች አስተባብለዋል። የፓሪስዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝሩን ልካልናለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ