1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአላሙዲና የኤልያስ መካሰስ

ረቡዕ፣ ጥር 4 2003

ከኢትዮጵያ ዉጪ የሚታተሙ የተለያዩ የኢትዮጵያዉያን አምደረቦች ደግሞ ከአቶ ኤልያስ ክፍሌ ጎን መቆማቸዉን እያስታወቁ ነዉ

https://p.dw.com/p/QrBn
ምስል Bilderbox

ኢትዮጵያዊ-ሳዑዲ አረቢያዊዉ ቱጃር ሼኽ መሐመድ አል-አሙዲ ኢትዮጵያን ሪቪዉ የተሰኘዉን ድረ-ገፅ አሳታሚ አቶ ኤሊያስ ክፍሌን በስም አጥፊነት ከሰዋል።ዩናይትድ ስቴትስ የሚሠሩና የሚኖሩት አቶ ኤሊያስ ክፍሌ የተከሰሱት ብሪታንያ ዉስጥ ነዉ።የክሱ ሒደት እስካሁን አልተጀመረም።የክሱ ምክንያትና ክሱ የተመሠረተበት ሥፍራ ግን እያነጋገረ ነዉ።ከኢትዮጵያ ዉጪ የሚታተሙ የተለያዩ የኢትዮጵያዉያን አምደረቦች ደግሞ ከአቶ ኤልያስ ክፍሌ ጎን መቆማቸዉን እያስታወቁ ነዉ።ሥለ ጉዳዩ የለንደኑን ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ