1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአለም የምግብ ቀን በሮማ

ሰኞ፣ ጥቅምት 6 2004

በሮማ -ኢጣሊያ ዛሬ አምስት ቀናት የሚቆይ የአለም የምግብ ጉባኤ ተከፈተ።ጉባኤው ትኩረቱን ያደረገው የምግብ ዋጋ መናር ላይ ሲሆን፤ የመሬት መቀራመትም ሌላው የመነጋገሪያው አጀንዳ ነው።

https://p.dw.com/p/RrOz
ምስል FAO

የጀርመን ግብርና ሚንስትር -ኢልዘ አይግነርም- ከጉባኤው ተካፋይ አንዷ ናቸው። ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ እንደሆነ፤ በጉባኤው ላይ እንደሚያሳስቡ ለዶይቸ ቬለ ጀርመንኛው ክፍል ገልፀዋል። በማደግ እና በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ባለፉት አመታት ብቻ ከ 50 እስከ 80 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለውጭ አገር ባለሀብቶች ሰጥተዋል። በሌላ በኩል በአለም ዙሪያ 925 ሚሊዮን ህዝብ በርሀብ እንደሚሰቃዩ የአለም የምግብና የግብርና ድርጅት ገልፀዋል። የኢዛ አይግነርን ቃለ መጠይቅ ከዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ