1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ክስና ኬንያ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 6 2003

የኬንያ የትምሕርት ሚንስትር፥ የኢንዲትሪ ሚንስትር፥ የራዲዮ ጣቢያ ሐላፊ፥ የካቢኔ ጉዳይ ሚንስትር እና የቀድሞ የፖሊስ ኮሚሽነር ከአንድ ሺሕ ሁለት መቶ በላይ ሰዎች ሕወት ለጠፋበት ወንጀልና መዘዙ ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/QcLC
ሞሬኖ ኦካምፖምስል AP

ኬንያ ዉስጥ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ2007 ማብቂያ የተደረገዉ የምርጫ ዉጤት ዉዝግብ በቀሰቀሰዉ ግጭት ለጠፋዉ ሕይወት፥ አካል፥ ሐብትና ንብረት ተጠያቂ ናቸዉ የተባሉ ስድስት የሐገሪቱ ባለ ሥልጣናት አለም አቀፉ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተጠየቀ።የፍርድ ቤቱ ጠቅላይ አቃቤ-ሕግ ሉዊስ ሞሬኖ ኦካምፖ ዛሬ ይፋ ባደረጉት መጥሪያ መሠረት የታገዱት የኬንያ የትምሕርት ሚንስትር፥ የኢንዲትሪ ሚንስትር፥ የራዲዮ ጣቢያ ሐላፊ፥ የካቢኔ ጉዳይ ሚንስትር እና የቀድሞ የፖሊስ ኮሚሽነር ከአንድ ሺሕ ሁለት መቶ በላይ ሰዎች ሕወት ለጠፋበት ወንጀልና መዘዙ ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች ናቸዉ።የኬንያ ባለሥልጣናት ግን ተጠያቂዎቹ እዚያዉ ኬንያ ዉስጥ ይዳኛሉ እያሉ ነዉ።ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት የናይሮቢዉን ወኪላችንን ዘሪሁን ተስፋዬን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ