1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኖርማንዲ ዘመቻ 70ኛ ዓመት

ዓርብ፣ ግንቦት 29 2006

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፣ አውሮፓን ከናዚ ጀርመን አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ተጎዳኝተው የዘመቱት አገሮች ፤ ከምዕራብ በኩል ከኢንግላንድ፤ በብዙ መርከቦችና ጀልባዎች ተሣፍረው ፈረንሳይ ኖርማንዲ ጠረፍ የገቡበት 70ኛ ዓመት በዛሬው ዕለት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ታስቦ ዋለ።

https://p.dw.com/p/1CE4X
D-Day Feier 06.06.2014 Gruppenfoto in Benouville
ምስል picture-alliance/AP Photo

20 ገደማ ከሚሆኑ አገሮች የተውጣጡ መሪዎች፤ የ88 ዓመቷ የብሪታንያ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ፤ የዩናይትድ ስቴትስና የሩሲያ ፕሬዚዳንቶች፤ ባራክ ኦባማና ቭላዲሚር ፑቲን እንዲሁም በዛ ያሉ ሌሎች የሀገር መሪዎች፤ በኖርማንዲ ጠረፍ ፣ ከ 70 ዓመት በፊት፤ እ ጎ አ ሰኔ 6 ቀን 1944 ዓ ም፤ በጀግንነት የተፋለሙትንና ሕይወታቸው ያለፈውን በማሰብ ፤ ከጦርነቱ ተርፈው ዛሬ በሽምግልና ዕድሜ በሥነ ሥርዓቱ ለተገኙት አርበኞች ልዩ ከበሬታ በማሳየትን ነው በዓሉን ያከበሩት። ፕሬዚዳንት ፑቲን የተጋበዙት፤ ከኖርማንዲው ጦርነት በፊት፣ በምሥራቅ በኩል የያኔዋ የሶቭየት ሕብረት ጦር ከሁሉ አስቀድሞ በናዚ ጀርመን ጦር ኃይል ላይ ድል በመቀዳጀቱ ነው።

በዛሬው በዓል፤ አንድ ሺ ገደማ የሚሆኑ በዚያ ቦታ የተዋጉ የቀድሞ ወታደሮች ተገኝተዋል። በጦርነቱ ለወደቁት ወታደሮች ከሐውልት ሥር ጉንጉን አበባ እንዲቀመጥ ተደርጓል። ንግሥት ኤልሳቤጥ፤ 5,000 ያህል የጋራ ንብረት ሃገራት ወታደሮች ባረፉበት መካነ መቃብር በተዘጋጀ ልዩ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተሳትፈዋል። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፤ «ኦማሃ ቢች» በተሰኘው የኖርማንዲ ጠርፍ ፤ በዚያ ከተገኙ ባለሜዳልያ የዚያ ዘመን ወታደሮች ፊት ባሰሙት ስሜታዊ ንግግር እንዲህ ነበረ ያሉት-

Merkel mit Putin und Poroschenko 06.06.2014 Benouville
ምስል Reuters

«ወደዚህ ተመልሼ በመምጣት፤ ማንኛውንም አደጋ ተጋፍጠው፤ መስዋእትነት ለከፈሉት ወንዶችና ሴቶች ተገቢውን በሬታ ስሰጥ ክብር ነው የሚሰማኝ። ርምጃ በተወሰደባት በዚያች ዕለት የተሰተፉ እንሆ በመካከላችን ይገኛሉ። የተከበራችሁ ፤ እዚህ በመገኘታችሁ በእውነት እንኮራለን።»

የአስተናጋጅ ሀገር የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ፍርንሷ ዖላንድ ፤ ለእንግዶቹ የምሳ ግብዣ እንዲዘጋጅ አድርገዋል።

በዩክሪይን ዉጥረት ሩስያ ከምዕራባዉያኑ ሃገራት ጋር የገባችዉ እሰጣ ገባ በመታሰብያ ዝግጅቱ ላይ ጥላ ያጠላበት ቢመስልም፤ በቃላት ሲጠዛጠዙ የነበሩት መሪዎች በክብረ በዓሉ ላይ በአንድ መድረክ በመቆም በጋራ ማዕድ ተቋድሰዋል፤ ዝርዝሩን የፈረንሳይዋ ወኪላችን ኃይማኖት ጥሩነህ አድርሳልናለች፤

ኃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ