1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርት

የንባብ ለሕይወት አውደ ርዕይ

ዓርብ፣ ሐምሌ 21 2009

በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል ከዛሬ አንስቶ እስከ ማክሰኞ የሚቆይ የመፅሐፍት ዓውደ ርዕይ ተጀምሯል። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ጸሐፍያን ፣ ደራሲያን እና በሺዎች የሚቆጠሩ የንባብ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/2h6eh
Symbolbild Literatur Bücherstapel
ምስል Fotolia/silver-john

«ንባብ ለሕይወት»

የ«ንባብ ለሕይወት» ዓውደ ርዕይ አዲስ አበባ ከተማ ላይ ሲካሄድ ዘንድሮ ሦስተኛ ጊዜው ነው። ለአምስት ቀናት የሚቆየውን ዓውደ ርዕይ ማዘጋጀት የጀመረው ቢንያም ከበደ ይባላል። ቢንያም ለኢትዮጵያ «FM» ጣቢያዎች በጋዜጠኝነት ያገለገ ሲሆን፤ ካለፉት 15 ዓመታት አንስቶ ደግሞ ትኩረቱን ወደ ትላልቅ ዝግጅቶች ቀይሯል። ከነዚህ መካከል ንባብ ለሕይወት የተሰኘው ፕሮጀክት አንዱ ነው።

Symbolbild Selbstverlag
በአውደ ርዕዩ ላይ በ«ሶፍት ኮፒ» መልክ የተዘጋጁ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ መጽሀፎች ለአንባቢያን በነጻ እንደሚቀርቡ ተገልጿል።ምስል Fotolia/Markus Bormann

በአውደ ርዕዩ ላይ ራሳቸውን ከሚያስተዋውቁት መካከል ተርጓሚ ህይወት ታደሰ አንዷ ናት።  በአሁኑ ወቅት የራሷን ድርሰት እየፃፈች ትገኛለች። በአውደ ርዕዩ ላይ ይዛ የምትቀርበው ደግሞ የትርጉም ሥራዋን ነው። ህይወት ከአንባቢነት ወደ ተርጓሚነት የተሸጋገረችው አንብባ የተረዳችውን ለሌሎች ለማሻፈል ስለምትሻ እንደሆነ ትናገራለች። እስካሁን የተረጎመቻቸው መጽሐፍት ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ነበሩ።

ዓውደ ርዕዩ ወጣቱ የእድሜ ክልል ላይ ቢያተኩርም ዘንድሮ ሁሉንም የእድሜ ክልል አንባብያን ያካተተ መሆኑን በንባብ ለህይወት ፕሪጀክት የመረጃ ክፍል ኃላፊ የሆነው ዬሴፍ ዳሪዎስ።ሕይወት ታደሰን ጨምሮ በርካታ ፀሀፊያን፣ ደራሲያን እና አንባቢያን በሚሳተፉበት እና ዓርብ በአዲስ አበባ በጀመረው ዓውደ ርዕይ ላይ እስከ 150 000 ሰዎች እንደሚሳተፉ አዘጋጆቹ ባለ ሙሉ ተስፋ ናቸው።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ