1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የናይጄሪያና የፈረንሳይ ፕሬዝደንቶች ዉይይት

ማክሰኞ፣ መስከረም 4 2008

የናጄሪያ መንግሥት በአሸባሪዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ቦኩ ሐራም ላይ የከፈተዉ ዘመቻ እንዲሳካ ፈረንሳይ ሙሉ ድጋፍዋን እንደምትሰጥ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ኦሎንድ አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/1GWyZ
Paris Treffen Buhari Hollande
ምስል Reuters/C. Hartmann

[No title]



ኦሎንድ ሐገራቸዉን ለሚገበኙት ለናጄሪያዉ አቻቸዉ ለመሐመዱ ቡኻሪ እንደነገሩት ከቦኮ ሐራም ጋር የሚደረገዉ ዉጊያ እራሱን የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት «ISIS»ብሎ ከሚጠራዉ ቡድን ጋር ከሚደረገዉ ዉጊያ የተለየ አይደለም። ፕሬዝደንት ቡኻሪም ለአስተናጋጃቸዉ እንደነገሩት ቦኩ ሐራም ከ«ISIS» ጋር ግንባር መፍጠሩን ካስታወቀ ወዲሕ የሚያደርሰዉ ጥቃት እየተጠናከረ ነዉ። የፓሪስዋ ወኪላችን ሐይማኖት ጥሩነሕ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች።

ሐይማኖት ጥሩነሕ

ነጋሽ መሃመድ
ኂሩት መለሰ