የናይጀሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫና ገዥው PDP
ዓርብ፣ ሚያዝያ 7 2003ማስታወቂያ
በአሁኑ ምርጫ ግን ፓርቲው ማሸነፍ ሊከብደው እንደሚችል ነው የሚገመተው ። የናይጀሪያ የምርጫ ኮሚሽን ከእንግዲህ ወዲያ ማጭበርበርን በቸልታ እንደማይመለከተው አስታውቋል ። ባለፈው ቅዳሜ በተካሄደው የህዝብ እንደራሴዎች ምርጫ ፓርቲው የያዘውን የምክር ቤት መቀመጫ እንዲቀንስ ተገዷል ። እስከ ትናንት በስተያ በተደረገው የመራጮች ድምፅ ቆጠራ ውጤት መሰረት PDP እስካሁን ይዞት የቆየውን ሁለት ሶሶተኛ አብላጫ ማጣቱ አይቀርም ። ፓርቲው ክርስቲያኑን ፕሬዝዳንት ጉድላክ ጆናታንን ለውድድር ማቅረቡ ደግሞ እያነገገረ ነው ። በሌላ በኩል የዶቼቬለ የሃውሳ ቋንቋ ክፍል ባልደረባ ቶማስ መሽ እንደዘገበው የአሁኑ የናይጀሪያ ምርጫ ሂደት ከቀደመው ምርጫ ጋር በንፅፅር ሲታይ የተሻለ መሆኑ እየተነገረ ነው ።
ቶማስ መሽ
ሂሩት መለሰ