1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሽብር ጥቃት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 22 2010

የዛሬ 16 ዓመት በሁለት የመንገደኛ አውሮፕላኖች ተገጭቶ እንዳልነበረ ከሆነው እና በሺህዎች የተገመቱ ሰዎች ካለቁበት የማንሀተኑ የቀድሞ የዓለም የንግድ ማዕከል መንትያ ሕንጻዎች አቅራቢያ ትናንት በተፈፀመው በዚሁ ጥቃት የ 8 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል ፤ ቢያንስ 11 ሰዎች ቆስለዋል።

https://p.dw.com/p/2ms5j
USA New York Autoanschlag in Manhattan
ምስል picture-alliance/New York Daily News/J. Keivom

ትናንት ከሰዓት በኋላ ኒውዮርክ ውስጥ በተከራየው መኪና ሆነ ብሎ እግረኞች እና በቢስክሌት ሲጓዙ የነበሩ ሰዎችን ገጭቶ በገደለው ሰው ላይ የሚካሄደው ምርመራ መቀጠሉ ተዘገበ። የአሜሪካን የፌደራል ምርመራ ቢሮ በምህጻሩ የኤፍ ቢ አይ ሠራተኞች በዲቪ ሎተሪ  ከኡዝቤክስታን ወደ አሜሪካን መግባቱ የተነገረውን የዚህን ግለሰብ መኖሪያ ቤት ዛሬ መፈተሻቸውን አሶስየትድ ፕሬስ ዘግቧል። የዛሬ 16 ዓመት በሁለት የመንገደኛ አውሮፕላኖች ተገጭቶ እንዳልነበረ ከሆነው እና በሺህዎች የተገመቱ ሰዎች ካለቁበት የቀድሞ የዓለም የንግድ ማዕከል መንትያ ሕንጻዎች አቅራቢያ ትናንት በተፈፀመው በዚሁ ጥቃት የ 8 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል ፤ ቢያንስ 11 ሰዎች ቆስለዋል። የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል።

መክበብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ