የኑሮ ዉድነትና የጠቅላይ ሚንስትሩ መግለጫ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 16 2003ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት በሐገሪቱ የንግድ ሥርዓት ዉስጥ በቀጥታ ጣልቃ መግባቱን እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አስታወቁ።ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ትናንት ነጋዴዎችን አዲስ አበባ ዉስጥ ሠብስበዉ እንደነገሩት አለቅጥ ያሻቀበዉን የሸቆጦች ዋጋ ንረት ለመቆጣጠር መንግሥት በቀጥታ በንግዱ መስክ ጣልቃ ይገባል።ነጋዴዎቹ የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት የነፃ ገበያን መርሕ የሚፃረር ነዉ በማለት ይቃወሙታል።ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ታደሰ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ